
ከተማ አስተዲደሩ ባለ ሀብቶችን በማስተባበር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ያስገነባቸውና በዛሬው እለት ያስመረቃቸው ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ማምረት ሲጀምሩ ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ዳቦ የማምረት አቅም ይኖራቸዋል።
ከንቲባ አዳነችን አቤቤ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ያስመረቅናቸው ሶስት የዳቦ ፋብሪካዎች በጥቅሉ በቀን ከ1ሚሊዮን በላይ ዳቦ ማምረት የሚችሉ ናቸው ያሉ ሲሆን፣ ይህም ለከተማችን ነዋሪዎች ትልቅ ትርጉም ያለው ሰው ተኮር ተግባር ነው ብለዋል።
ከማህበረሰቡ ጋር ማደግ፣ ካለን ማካፈል፣ በጋራ መስራት፣ በጋራ ተጠቃሚ መሆንን መሬህ አድርጋችሁ አነዚህን የዳቦ ፋብሪካዎች ያቋቋማችሁ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል። ከተማ አስተዳደሩ መሬት አቀረበ፣ ባለሀብቶቹ ደግሞ ኢንቨስት አድርገው ህዝቡ እንዲጠቀም ትልቅ ስራ ተሰርቷልም ብለዋል።
ከንቲባ አዳነች አክለውም የከተማ አስተዳደሩ መሰል ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ህብረተሰቡን፣ ባለሀብቶችን እና በጎፍቃደኞችን በማስተባበር የህዝቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማው ዛሬ በከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተመረቁት 3 የዳቦ ፋብሪካዎች በተጨማሪ
= የ5 የጤና ጣቢያ እድሳት ግንባታዎች
= የ10 ትምህርት ቤቶች ማስፋፊያ ግንባታ
= የ2 ወጣት ማዕከላት ሙሉ እድሳት
= የ3 ፖሊስ ካምፖች ተጨማሪ ግንባታ
= የ3 ሼዶች ግንባታ (ከ300 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች መስሪያ ቦታ)
= 1 መደመደመር ትውልድ የስፖርት ማዘወተሪያና የህፃናት መጫወቻ ማዕከል
= የ1 ቤተመጻህፍት ሙሉ እድሳት
= የ9ኝ ወረዳዎች የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ፅ/ቤቶች ማዘመን ይገኙበታል።
ኑ ሁሌም ልናገለግሎ ዝግጁ ነን!!
የኮልፌ ክ/ከተማ የወረዳ 10 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቃሲም ሱሩር ከመንግስት ቤቶች እና የደንብ ማስከበር አመራሮች ጋር በመሆን በወረዳው የሚገኙ ነዋሪዎችም የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚዉ የተገልጋዩ ጥያቄ እየመለሱ ችግሮቹ የሚፈቱበት አቅጣጫ እያስቀመጡ ይገኛሉ።
Hi, this is a comment.
To get started with moderating, editing, and deleting comments, please visit the Comments screen in the dashboard.
Commenter avatars come from Gravatar.